ይኩኖ አምላክ

(ከይኵኖ አምላክ የተዛወረ)


ዓፄ ይኩኖ አምላክ (የዘውድ ስም ተስፋ እየሱስ) ከነሐሴ ፫ ቀን ፲፪፻፵፭ ዓ/ም ጀምሮ ለ አሥራ አምስት ዓመታት ነግሠዋል። በአባታቸው በተስፋ እየሱስ በኩል ከዛግዌ ስርወ መንግስት መነሳት በፊተ ከነበሩት የአክሱም ንጉስ የአጼ ድል ናኦድ ጋር እንደሚዛመዱ ይጠቀሳል። [1]

ዓፄ ይኩኖ አምላክ
ይኩኖ አምላክ
ይኩኖ አምላክ
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛትከ፲፪፻፵፭ ዓ/ም - ፲፪፻፷ ዓ/ም
ተከታይዓፄ ይግባ ጽዮን
ሙሉ ስምቀዳማዊ ሰለሞን
ሥርወ-መንግሥትሰሎሞን
አባትተስፋ እየሱስ
የተቀበሩትደጋ እስጢፋኖስደጋ ደሴት
ሀይማኖትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ

ይኩኖ አምላክ ማለት አምላክ ጠባቂና ረዳት ይሁነው ሲሆን የተወለዱበትም እዚያው ወሎ ውስጥ ከደሴ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ሰገርት የምትባል ከተማ ነበር። ትህምህርታቸውንም ያጠናቀቁት ከአምባሰል ቀረብ ብሎ በሚገኘው ሃይቅ በሚባለው አካባቢ በ ሃይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ነበር። ትምህርታቸውን በቅዱስ እየሱስ ሞዓ ወይም በቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ወይም በሁለቱ ስር እንደወሰዱ የተጻፉ የተለያየ ዘመን ገድላቶች አሉ። ይሁንና የዛግዌን ስርወ መንግስት በሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ከትምህርታቸው መገባደድ በኋላ ወይ በጦርነት ወይ በሰላም እንደቀየሩ ታሪክ ይመዘግባል።

ይኩኖ አምላክ በባልደረባወቹና በአረቦች ሲጠበቅ የሚያሳይ ጥንታዊ ስዕል

ምንም በማያጠረጣር ሁኔታ፣ ጸሃፊው ዋሊስ በድጅ እንደመዘገበ፣ ይኩኖ አምላክ ከቢዛንታይን ንጉስ ሚካኤል 8ኛ ጋር ደብዳቤ ተቀያይሯል እንዲሁም ለቤዛንታይኑ ንጉስ ብዙ ቀጭኔወችን በስጦታ እንደላከ አሁን ድረስ ማስረጃ አለ። [2] ለግብጹ ማምሉክ ሱልጣን ባይባርስም ከእስክንድርያ ፓትሪያርክ ሾሞ እንዲልክለት በ1273 በተደጋጋሚ እንደጻፈ ታሪክ መዝግቦ አልፏል። የተፈገውም ጳጳስ በጊዜው ስላለመጣ ከጎረቤት እስላም መሪወች በመጀመሪያው የመንግስቱ ዘመን የነበረው ስለማዊ ግንኙነት ተቋረጠ።

ቀጥሎም የ ቆብጥ ፓትሪያርክ ባለመምጣቱ ይኩኖ አምላክ ወደ ሶሪያ ቄሶች እንዳዘነበለ ታደሰ ታምራት መዝግቧል። [3] እናም በዚህ ንጉስ ዘመን ከግብጾች ይልቅ የሶሪያወች ተሳትፎ በቤተክርቲያን ዙሪያ ይታይ ነበር።

ወሎ ውስጥ፣ ገነተ ማርያም የተሰኘውን ቤ/ክርስቲያን ያሰሩ እኒሁ ንጉስ ናቸው[4] ። ባረፉ ጊዜ የተቀበሩትም ደጋ ደሴት ተብላ በምትታወቀው የጣና ሃይቅ ደሴት ውስጥ የወንድማቸው ልጅ ሂሩተ አምላክ ባሰራው ደጋ እስጢፋኖስ ነው።

ማጣቀሻዎችለማስተካከል

  • ^ In the Ethiopian calendar, 10 Sené and 16 Nehasé, respectively. A. K. Irvine, "Review: The Different Collections of Nägś Hymns in Ethiopic Literature and Their Contributions." Bulletin of the School of Oriental and African Studies, University of London. School of Oriental and African Studies, 1985.
  • ^ ዋሊስ በድጅ, A History of Ethiopia: Nubia and Abyssinia, 1928 (Oosterhout, the Netherlands: Anthropological Publications, 1970), p. 285.
  • ^ ታደሰ ታምራት, Church and State, pp. 69ff.
  • ^ Paul B. Henze, Layers of Time, A History of Ethiopia (New York: Palgrave, 2000), p. 59.

  • 🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchአበበ ቢቂላአንኮር ዋትሥርዓተ ነጥቦችላሊበላየአድዋ ጦርነትየአክሱም ሐውልትዓፄ ቴዎድሮስቅዱስ ያሬድጥላሁን ገሠሠእርዳታ:ይዞታኢትዮጵያቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴየዋና ከተማዎች ዝርዝርModule:Argumentsአፈወርቅ ተክሌአስቴር አወቀአክሱምዳግማዊ ምኒልክኢንዶኔዥያሥነ ምግባርኤችአይቪገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችምሥራቅ አፍሪካአዲስ አበባየጢያ ትክል ድንጋይሙላቱ አስታጥቄጣይቱ ብጡልደራርቱ ቱሉጥሩነሽ ዲባባሐረርገብርኤል (መልዐክ)ጀጎል ግንብአማርኛፋሲል ግቢየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማጥርኝኃይሌ ገብረ ሥላሴቅዱስ ገብርኤልውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌዘጠኙ ቅዱሳንቴሌቪዥንፀደይየኢትዮጵያ ቋንቋዎችመጽሐፍ ቅዱስየጋብቻ ሥነ-ስርዓትማሪቱ ለገሰአክሊሉ ለማ።የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችአሊ ቢራአፈ፡ታሪክትግራይ ክልልዩ ቱብአስናቀች ወርቁዐቢይ አህመድየኢትዮጵያ አየር መንገድየኢትዮጵያ ነገሥታትማርያምልዩ:RecentChangesየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርኬንያየቅርጫት ኳስክረምትፋሲለደስየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግአሸንዳበጋፍቅርሥነ-ፍጥረትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንሀዲያዛጔ ሥርወ-መንግሥትየዮሐንስ ወንጌልዮሐንስ ፬ኛጸጋዬ ገብረ መድህንአማራ (ክልል)ስዕል:Tewodros.Fusela.pdfታሪክመሬትግብረ ስጋ ግንኙነትየኢትዮጵያ ሕገ መንግስትአክሱም መንግሥትየቃል ክፍሎችቅኔንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያእምስብጉንጅጥግእያሱ ፭ኛበላይ ዘለቀባሕልኢየሱስኦሮሞውክፔዲያሀዲስ ዓለማየሁገዳዩ ባልሽ የሞተው ወንድምሽስዕል:Tewodros.Mondon.pdfሚካኤል