የሠገራ ትቦ ንጣፍ መድማት ወይመ መቁስል (ሄሞሮይድ)

መግቢያ

የሠገራ ትቦ ንጣፍ / ፊንጢጣ (ሄሞሮይድ) በሠገራ ትቦ ዙሪያ የተነጠፈ ከደም ቅዳና ከደም መልስ ትቦዎችና ከአገናኝ ጅማቶች የተፈጠረ ሲሆን ሠገራን ለመቆጣጠር ይረዳል። የሠገራ ትቦ ንጣፍ መድማት፣ መቁሰል ወይም ማበጥ ለህመም ስሜትን መንስኤ ይሆናል። የሄሞሮይድ የበሽታ ምልክት እንደበሽታው አይነት ይለያያል። ውስጣዊ ሄሞሮይድ በአብዛኛው ከሠገራ ትቦ መድማት ጋር ሲያያዝ ፡ ውጫዊ ሄሞሮይድ በፊንጢጣ አካባቢ ከሚመጣ የህመም ሥሜት (መቁሰል) ጋር ይያያዛል።

ሄሞሮይድን ለመከላላከል ስራስር (ክር) የያዙ ምግቦችን በብዛት መመገብ፣ ውሃ በብዛት መጠጣት፣ ፊንጢጣን በንፁህ ውሃ ማጠብ (መዘፍዘፍ)፣ እረፍት ማድረግ፣ ቁስለትን (ጥዝጣዜን) ለመከላከል የሚረዱ (ነን ስቴሮይዳል አንቲ ኢንፍላማቶሪ) መድሃኒቶችን መጠቀም ይመከራል። በእነኚህ መንገዶች በሽታውን መቀነስ ላልቻሉ ህመምተኞች የቀዶ ጥገና ሌላው አማራጭ ነው።