አማራ (ክልል)

(ከአማራ ክልል የተዛወረ)
አማራ ክልል
ክልል
የአማራ ክልልን በቀይ የሚያሳይ የኢትዮጵያ ካርታ
አገርኢትዮጵያ
ርዕሰ ከተማባህር ዳር
የቦታ ስፋት
   • አጠቃላይ194,709[1]
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ35,875,702[1] (25,987,678 በአማራ ክልል እሚኖር ሲሆን የተቀረው በሌላው የሀገሬቱ ክፍል ይኖራል)
  • 'አማራ(ነፃ-ህዝብ:ጨዋ:ኩሩ) (ክልል 3) ከዘጠኙ ከኢትዮጵያ ክልሎች አንዱ ሲሆን አራት የሀገሪቱን ዋና ወና ክፍለ ሀገራት ያካትታል እነሱም ጎንደር:ጐጃም:ቤተ-አምሓራ(ወሎ)እና ሸዋ ናቸው።የአማራ ብሔራዊ ክልል ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ በ8° 45 እስከ 13° 45 ሰሜን የኬንትሮስ እና በ35° 46 እስከ 40° 25 ምስራቅ የኬንትሮስ መስመር ውስጥ ይገኛል። በምስራቅ የአፋር፣ በምዕራብ ሱዳን እና ቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል፣ በሰሜን የትግራይ ክልልና ኤርትራ በደቡብ የኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል። የቆዳ ስፋቱ ፻፶፯ሺ፸፮ ካሬ ሜትር ሲሆን ከአገሪቱ አሥራ አምስት በመቶ ድርሻ ይይዛል። የክልሉ ሕዝብ ብዛት ደግሞ በ፳፻፪ ዓ/ም 20,875,456 እንደነበር የተገመተ ሲሆን አንዳንድ ደግሞ ከ 40 ሚልዮን ሕዝብ በላይ እንደሆነ ይናገራሉ (49 %) ከአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ 33.9% አካባቢ ድርሻ ይይዛል ተብሎ ይገመታል። ክልሉ በ፲ ዞኖችና በ፻፷፮ የገጠርና የከተማ ወረዳ አስተዳደሮች የተከፋፈለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ፴፰ የሚሆኑት የከተማ አስተዳደሮች ናቸው።የአማራ፣የአገው፣የኦሮሞና የሌሎች ብሔረሰቦች በጋራ የሚኖሩበት ክልል ነው።እንዲሁም የአማራ ክልል አሁን ላይ የክልል ከተማው ባህር ዳር ነው አማራ ማለት ጀግና የጀግና ልጅ ነው ለምሳሌነት አጤ ቴዎድሮስ፣በላይ ዘለቀ፣እምየ ምኒልክ፣ንጉሥ ሚካኤል እነዚህ በዋናነት ይጠቀሳሉ እንጂ ብዙዎችን ማውሳት ይቻላል

የተፈጥሮ ሀብትለማስተካከል

  1. በክልሉ አልፎ አልፎ ከሚታዩ የመንግሥትና የማኅበራት ደኖች፣ በደሴቶች፣በአብያተ ክርስቲያናት፣ በወንዞች ዳርቻና ሰው ሊደርስባቸው በማይችሉ ገደላማ ቦታዎች እንዲሁም ተራራማ ስፍራዎች ለምሳሌ ራስ ዳሽን፣ጉና ተራራ፣ጮቄ ተራራ ከሚገኙ ጥቂት ደኖች በስተቀር ሊጠቀስ የሚችል ከፍተኛ የደን ሀብት ጋር በቅርብ የተያያዘ ነው። በዚህ ረገድ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ እንደ ቀይ ቀበሮዋልያጭላዳ ዝንጀሮ እንዲሁም በምዕራባዊው የክልሉ አካባቢ ዝሆን አንበሳነብርሰጐንና የተለያዩ አዕዋፋት በስተቀር ከፍተኛ የዱር እንስሳት ክምችት ካለመኖሩም በላይ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ጥቂት የደን ቅሪቶችና ዋሻዎች የነበሩት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አራዊቶችም ለዘመናት በደረሰው የደን መጨፍጨፍና መራቆት ምክንያት ከክልሉ ወደ ሌላ አካባቢ እንደተሰደዱ ይታወቃል።
  2. 2.የክልሉን የማዕድን ሀብት አስመልክቶ በሚገባ የተጠናከረ ጥናት ባይኖርም ከክልሉ ስነ-ምድራዊ ሁኔታዎችና ከተካሄዱ አንዳንድ ጠቋሚ ጥናቶች መረዳት እንደሚቻለው በክልሉ ውስጥ የተለያዩ ማዕድናት እንደአሉ ይገመታል። በዚህም መሠረት በሰሜን ሸዋ የኦፓል ማዕድን፣ በሰሜን ጐንደር፣ በጭልጋና በደቡብ ወሎአምባሰል ወረዳ የድንጋይ ከሰል ክምችት እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ለግንባታ ሥራ የሚውል በቂ የድንጋይ፣ የኖራ ድንጋይ፣የሸክላ አፈር፣ ጅኘሲየም፣ የጌጣጌጥ ማዕድናት እንዲሁም በዓባይ ሸለቆ የዕብነ በረድ ሐብቶች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይሁን እንጅ በውል የሚታወቀው ሐብትም ቢሆን በበቂ ሁኔታ አልለማም።

የውሀ ሀብትለማስተካከል

ክልሉ የትልልቅ ወንዞች ባለቤት ሲሆን በአጠቃላይ በሦስት ዋና ዋና ተፋሰሶች ተከፋፍሎ ሊታይ የሚችል ነው። እነርሱም የዓባይ፣ የርብ፣የብር ወንዝ ፣የአንገረብ ፣የጭዬ፣የየጀማ፣የተከዜ እና የአዋሽ ተፋሰስ ናቸው። ወደነዚህ ተፋሰሶች የሚገቡና ዓመቱን በሙሉ የማይደርቁ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ትልልቅ ወንዞች ያሉ ሲሆን በክልሉ በጥቅም ላይ ያልዋለ ሰፊ የውሐ ሀብት መኖሩን ያመለክታሉ። ከነዚህ በተጨማሪ እንደ ጣና፣አርዲቦ፣ሀይቅ፣ዘንገና እና የመሳሰሉ ሐይቆችም በክልሉ ውስጥ ይገኛሉ። በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ ባሉ ትልልቅ ወንዞችና መጋቢ ወንዞች የመስኖ ልማት ለማካሄድ የሚያስችል ከፍተኛ የውሐ ሐብት ክምችት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጅ እስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋለው በጣም አነስተኛ ነው።

ምጣኔ ሀብትለማስተካከል

በአመዛኙ አብዛኛው የክልሉ ምጣኔ ሀብት በግብርና እና ከብት እርባታ ላይ የተመሠረተ ነው። በአጠቃላይ ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ቁጥር፣ ለእርሻና ለእንስሳት እርባታ ተስማሚ የሆነ መሬት፣ የአየር ንብረት እና የውሐ ሀብቶች ያሉት በመሆኑ በተለይም የሰብል እና የእንስሳት ሀብት ልማት ለማካሄድ የማይናቅ አቅም አለው። በዝናብም ሆነ የመስኖ እርሻ ልማት በማስፋፋት በክልሉ በገበያ የሚውሉ የተለያዩ የአገዳ፣ የጥራጥሬ፣ የቅባት፣የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎችን ማምረት ይቻላል። ሩዝ፣ግብጦ፣ዘንጋዳ፣ማሾ፣ደልጎም፣አደንጓሬ፣ቦለቄ፣ጤፍ፣ ገብስ፣በቆሎ፣ ማሽላ፣ዳጉሣ፣ ስንዴ፣አተር፣ ባቄላ፣ ሽምብራ፣ ጓያ፣ምስር፣ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ተልባ፣ሱፍ ፣ኑግ፣አኩሪ አተር ወዘተ የመሳሰሉት በክልሉ ውስጥ ከሚመረቱ ሰብሎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በእንስሳት ሀብት ረገድም በወተት ምርታማነታቸው የታወቁ የፎገራ ዝርያዎችና በፀጉር ምርት የታወቁት የመንዝ በግ ዝርያዎች በክልሉ ይገኛሉ።

የጎብኚዎች መስሕብለማስተካከል

በቱሪዝም የሥራ መስክ ሊበለጽጉ ፣በሰፊው አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ እና በዓለም የቅርስ መዝገብ የሰፈሩት የጣና ደሴት ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ፣የጐንደር ቤተ መንስግት ህንፃዎች ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣በሸዋ ግዛት አንኮበር ወረዳ የሚገኘው የዳግማዊ ሚኒሊክ ቤተመንግሥት ፣ጥንታዊቷ የመርጡ ለማርያም ገዳም ፣የሾንኬ ጥንታዊ መንደር እና መስጊድ፣ የጥሩሲና መስጊድ፣የምስራቅ አፍሪካ የውሀ ማማ ተብሎ የሚጠራው ጮቄ ተራራ ፣ጭስ አባይ ፏፏቴ ፣ይስር ፋፋቴ ፣የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቱሪዝም መስሕቦች አሉት፣ ይሁን እንጅ ክልሉ ሰፊ የሆነ የቱሪዝም እምቅ ሀብት ያለው ቢሆንም በሚፈለገው መጠን በጥቅም ላይ ውሏል ማለት አያስደፍርም። በዚህ ረገድ፤አካባቢዉ የብዙ ታሪካዊ ገዳማትና የታሪካዊ ቅርሶችም ባለሀብት ነው።

ዋቢ ምንጭለማስተካከል

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ድረ-ገጽ፤ «የክልሉ አጠቃላይ ገጽታ» በ21 Dec 2012 እ.ኤ.አ. የተቃኘ

  1. ^ "፳፻፬ ዓ.ም. ብሔራዊ ስታቲስቲክስ". ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ. Archived from the original on 2015-09-23. በሰኔ ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የተወሰደ.


ኢትዮጵያ

ታሪካዊ ቦታዎች - አክሱም | ላሊበላ | ጎንደር | ነጋሽ | ሐረር | ደብረ-ዳሞ | አዲስ አበባ
አስተዳደራዊ ክልሎች - ትግራይ | አፋር | አማራ | ኦሮሚያ | ሶማሌ | ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል | ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች | ጋምቤላ | ሐረሪ | አዲስ አበባ | ድሬዳዋ
ቋንቋዎች - አማርኛ | ግዕዝ | ኦሮምኛ | ትግርኛ | ጉራጊኛ | ሶማሊኛ | አፋርኛ | ሲዳምኛ | ሃዲያኛ | ከምባትኛ | ወላይትኛ | ጋሞኛ | ከፋኛ | ሃመርኛ | ስልጢኛ | ሀደሪኛ
መልክዓ-ምድር - አባይ | አዋሽ | ራስ-ዳሽን | ሶፍ-ዑመር | ጣና | ደንከል | ላንጋኖ | አቢያታ | ሻላ
ከተሞች - የኢትዮጵያ ከተሞች

🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchአበበ ቢቂላአንኮር ዋትሥርዓተ ነጥቦችላሊበላየአድዋ ጦርነትየአክሱም ሐውልትዓፄ ቴዎድሮስቅዱስ ያሬድጥላሁን ገሠሠእርዳታ:ይዞታኢትዮጵያቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴየዋና ከተማዎች ዝርዝርModule:Argumentsአፈወርቅ ተክሌአስቴር አወቀአክሱምዳግማዊ ምኒልክኢንዶኔዥያሥነ ምግባርኤችአይቪገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችምሥራቅ አፍሪካአዲስ አበባየጢያ ትክል ድንጋይሙላቱ አስታጥቄጣይቱ ብጡልደራርቱ ቱሉጥሩነሽ ዲባባሐረርገብርኤል (መልዐክ)ጀጎል ግንብአማርኛፋሲል ግቢየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማጥርኝኃይሌ ገብረ ሥላሴቅዱስ ገብርኤልውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌዘጠኙ ቅዱሳንቴሌቪዥንፀደይየኢትዮጵያ ቋንቋዎችመጽሐፍ ቅዱስየጋብቻ ሥነ-ስርዓትማሪቱ ለገሰአክሊሉ ለማ።የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችአሊ ቢራአፈ፡ታሪክትግራይ ክልልዩ ቱብአስናቀች ወርቁዐቢይ አህመድየኢትዮጵያ አየር መንገድየኢትዮጵያ ነገሥታትማርያምልዩ:RecentChangesየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርኬንያየቅርጫት ኳስክረምትፋሲለደስየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግአሸንዳበጋፍቅርሥነ-ፍጥረትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንሀዲያዛጔ ሥርወ-መንግሥትየዮሐንስ ወንጌልዮሐንስ ፬ኛጸጋዬ ገብረ መድህንአማራ (ክልል)ስዕል:Tewodros.Fusela.pdfታሪክመሬትግብረ ስጋ ግንኙነትየኢትዮጵያ ሕገ መንግስትአክሱም መንግሥትየቃል ክፍሎችቅኔንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያእምስብጉንጅጥግእያሱ ፭ኛበላይ ዘለቀባሕልኢየሱስኦሮሞውክፔዲያሀዲስ ዓለማየሁገዳዩ ባልሽ የሞተው ወንድምሽስዕል:Tewodros.Mondon.pdfሚካኤል