ቁጥር

ቁጥር ፦ ለመቁጠር ወይም ደግሞ ለመለካት የምንጠቀምበት የሂሳብ ቁስ ነው። ቁጥሮች ከዚህ ከሁለቱ ጥቅማቸው ውጭ በአሁኑ ጊዜ ለልዩ ልዩ ጥቅም ይውላሉ። ለምሳሌ፦ አንድን ነገር ለመለየት (ምሳሌ ስልክ ቁጥር)፣ ለመደርደር (ሲሪያል ቁጥር)፣ ኮድ ለማበጀት (ISBN ቁጥር) ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው።

አንድንድ ሂደቶች አንድ ወይም ሁለት ቁጥሮችን ወስደው ሌላ ቁጥርን ይሰጡናል። እኒህ ሂደቶች ኦፕሬሽን ይባላሉ። ለምሳሌ ቁጥር ሲስጠን ቀጣዩን ቁጥር የምናገኝ ከሆነ ይህ ሂደት ቀጣም በመባል ይታወቃል፣ የሚወስደውም ቁጥር ብዛት አንድ ብቻ ስለሆነ ዩናሪ ኦፐሬሽን ይባላል። እንደ መደመር፣ መቀነስና፣ ማባዛት፣ ማካፈል ያሉት ደግሞ ባይናሪ ኦፕሬሽን ይባላሉ። እንደዚህ ያሉትን የቁጥር ኦፕሬሽን የሚያጠናው የሂሳብ ክፍል ሥነ ቁጥር ወይም አርቲሜቲክ (በእንግሊዝኛ Arithmetic) ይሰኛል።

የቁጥሮችን ቁመና በግሩፕ፣ ቀለበት ና ሜዳ የሚያጠናው የሂሳብ ክፍል የነጠረ አልጀብራ ተብሎ ይታወቃል።

ቁጥር አይነቶች
የተፈጥሮ ቁጥሮች0, 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, ..., n
ኢንቲጀር ቁጥሮች-n, ..., -8, -4, -3, -2, -1, 0, 1, 2, 3, 4, 5, ..., n
ፖዘቲቭ ኢንቲጀሮች1, 2, 3, 4, 5, ..., n
ራሽናል ቁጥሮችa/b where a and b are integers and b is not zero
እውን ቁጥሮችA rational number or the limit of a convergent sequence of rational numbers
ያቅጣጫ ቁጥሮችa + bi where a and b are real numbers and i is the square root of -1

የቁጥር ምልክቶችለማስተካከል

የሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥሮች ምልክቶች (0123456789) በዘመናዊ ቅርጾቻቸው በአውሮፓ ከ1550 ዓም ግድም ጀምሮ ነው። ከዚያ በፊት በነባሮች ቅርጾቻቸው በአውሮፓ ከ968 ዓም ጀምሮ ይታወቁ ነበር። እነርሱም ከአረብኛ ቁጥሮች ተወሰዱ። አረቦችም የሕንድ ቁጥሮች የበደሩ ከ768 ዓም ጀምሮ ነበር። የአረብ ሊቃውንት ከአውሮፓ ሊቃውንት በነዚህ ፪ መቶ አመታት በዜሮ (0) ጥቅም ቅድምትነታቸው ምክንያት፣ በሥነ ቁጥር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሳይንስ ዘርፎች ሥነ ቁጥሮች በመቀለላቸው በኩል፣ ለጊዜው የአረብ አለም ሊቃውንት በይበልጥ ለመግፋት ቻሉ። ሕንዶችም የዜሮ ጥቅም ያወቁት ቢያንስ ከ620 ዓም ጀምሮ ነበር። ለያንዳንዱ ሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥር ምልክት አደረጃጀት፣ በየአማርኛ ስሙ አንድ ሁለት ሦስት አራት አምስት ስድስት ሰባት ስምንት ዘጠኝ ይዩ።

ግዕዝ ቁጥሮች ምልክቶች በቀጥታ ከግሪክ ፊደል ቁጥሮች ተበደሩ፤ እንዲሁ፦

123456789102030405060708090100
ግሪክኛΑΒΓΔΕϚΖΗΘΙΚΛΜΝΞΟΠϘΡ
ቅብጥኛϤ
ቢዛንስαβγδεϚζηθικλμνξοπϟρ
ግዕዝ

ይህ የግሪኮች ዘዴ የተለማ ምናልባት 400 ዓክልበ. ግድም ሲሆን፣ ከዚያ ቀድሞ ሌላ የአቆጣጠር ዘዴ ለግሪኮቹ ነበራቸው። የግዕዝ ቁጥር ቅርጾች ከ500 ዓም ያህል ጀምሮ ናቸው (የአባ ገሪማ ብራናዎች)።

በአውሮፓ ከሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥሮች በፊት የነበረው ዘዴ ሮማዊ ቁጥሮች በአንዳንድ ቦታ እስካሁን ይገኛል። በዚህም፦

  • I = ፩ ፣ II = ፪ ፣ III = ፫
  • IV = ፬ ፣ V = ፭ ፣ VI = ፮ ፣ VII = ፯ ፣ VIII = ፰
  • IX = ፱ ፣ X = ፲ ፣ XI = 11 ወዘተ.
  • XX = ፳ ፣ XXX = ፴
  • XL = ፵ ፣ L = ፶ ፣ LX = ፷
  • XC = ፺ ፣ C = ፻ ፣ CC = ፪፻ ፣ CCC = ፫፻
  • CD = ፬፻ ፣ D = ፭፻ ፣ DC = ፮፻ ወዘተ.
  • CM = ፱፻ ፣ M = ፲፻ ፣ MC = ፲፩፻

እነዚህ ቅርጾች እንደ ላቲን አልፋቤት ፊደላት I, V, X, L, C, D, M ለመምሰል የጀመሩ ከ1 ዓም አካባቢ ነው። ሆኖም በውነት ከጥንታዊ ኤትሩስክኛ ቁጥሮቹ ምልክቶች («𐌠, 𐌡, 𐌢, ⋔, 𐌚, ⊕» ለ«I, V, X, L, C, M») የተለሙ ናቸው።

ከነዚህ ዘዴዎች በቀር በጣም ብዙ ሌሎች የአቆጣጠር ምልክቶች ዘዴዎች ከቦታ ወደ ቦታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለያዩ በሰው ልጆች ታሪክ ላይ ተገኝተዋል።

🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchአበበ ቢቂላአንኮር ዋትሥርዓተ ነጥቦችላሊበላየአድዋ ጦርነትየአክሱም ሐውልትዓፄ ቴዎድሮስቅዱስ ያሬድጥላሁን ገሠሠእርዳታ:ይዞታኢትዮጵያቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴየዋና ከተማዎች ዝርዝርModule:Argumentsአፈወርቅ ተክሌአስቴር አወቀአክሱምዳግማዊ ምኒልክኢንዶኔዥያሥነ ምግባርኤችአይቪገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችምሥራቅ አፍሪካአዲስ አበባየጢያ ትክል ድንጋይሙላቱ አስታጥቄጣይቱ ብጡልደራርቱ ቱሉጥሩነሽ ዲባባሐረርገብርኤል (መልዐክ)ጀጎል ግንብአማርኛፋሲል ግቢየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማጥርኝኃይሌ ገብረ ሥላሴቅዱስ ገብርኤልውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌዘጠኙ ቅዱሳንቴሌቪዥንፀደይየኢትዮጵያ ቋንቋዎችመጽሐፍ ቅዱስየጋብቻ ሥነ-ስርዓትማሪቱ ለገሰአክሊሉ ለማ።የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችአሊ ቢራአፈ፡ታሪክትግራይ ክልልዩ ቱብአስናቀች ወርቁዐቢይ አህመድየኢትዮጵያ አየር መንገድየኢትዮጵያ ነገሥታትማርያምልዩ:RecentChangesየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርኬንያየቅርጫት ኳስክረምትፋሲለደስየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግአሸንዳበጋፍቅርሥነ-ፍጥረትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንሀዲያዛጔ ሥርወ-መንግሥትየዮሐንስ ወንጌልዮሐንስ ፬ኛጸጋዬ ገብረ መድህንአማራ (ክልል)ስዕል:Tewodros.Fusela.pdfታሪክመሬትግብረ ስጋ ግንኙነትየኢትዮጵያ ሕገ መንግስትአክሱም መንግሥትየቃል ክፍሎችቅኔንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያእምስብጉንጅጥግእያሱ ፭ኛበላይ ዘለቀባሕልኢየሱስኦሮሞውክፔዲያሀዲስ ዓለማየሁገዳዩ ባልሽ የሞተው ወንድምሽስዕል:Tewodros.Mondon.pdfሚካኤል