ሴኔጋል

ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል። የጋምቢያ ግዛት እንዳለ በሴኔጋል ውስጥ ነው የሚገኘው። የሴኔጋል የቆዳ ስፋት 197,000 ካሬ ኪ.ሜ. የሚጠጋ ሲሆን የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ ወደ 17 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። የሴኔጋል የአየር ሁኔታ የየምድር ወገብ ሲሆን ደረቅና ዝናባማ ወራት ተብሎ ወደ ሁለት ይከፈላል።

የሴኔጋል ሪፐብሊክ
République du Sénégal

የሴኔጋል ሰንደቅ ዓላማ የሴኔጋል አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Pincez Tous vos Koras, Frappez les Balafons
የሴኔጋልመገኛ
የሴኔጋልመገኛ
ሴኔጋል በቀይ ቀለም
ዋና ከተማዳካር
ብሔራዊ ቋንቋዎችፈረንሳይኛ
መንግሥት

ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
ፕሬዝዳንታዊ-ረፐብሊክ
ማኪ ሳል
ሞሐመድ ዲየን
ዋና ቀናት
መጋቢት ፳፮ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም.
(April 4, 1960 እ.ኤ.አ.)
 
ነፃነት ከፈረንሳይ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
196,712 (86ኛ)
2.1
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2016 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
15,589,485 (72ኛ)
14,320,055
ገንዘብCFA ፍራንክ
ሰዓት ክልልUTC +0
የስልክ መግቢያ221
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ.sn

የሴኔጋል ርዕሰ ከተማ ዳካር በሀገሩ የምዕራብ ጫፍ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። ከባህር ጠረፍ ወደ ፭፻ ኪ.ሜ. ገደማ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የኬፕ ቨርድ ደሴቶች ይገኛሉ። በ፲፯ኛው ና ፲፰ኛው ክፍለ ዘመናት በቅኝ ገዢ መንግሥታት የተሠሩ የንግድ ተቋማት ከባህር ዳር ይገኛሉ።

ታሪክለማስተካከል

በአካባቢው ያሉ ግኝቶች ሴኔጋል ከጥንት ጀምሮ የሚኖርበት እንደነበረ ያሳያሉ። እስልምና የአካባቢው ዋና ሀይማኖት ሲሆን ወደ ሴኔጋል የተዋወቀውም በ11ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታመናል። በ13ኛውና 14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የማንዲንጎ ግዛት በአካባቢው ላይ ተጽኖ ያደርግ ነበር። በዚሁም ጊዜ ነው የጆሎፍ ግዛት የተመሠረተው። በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋልኔዘርላንድስ እና ኢንግላንድ በአካባቢው ለመነገድ ይወዳደሩ ነበር። በ1677 እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ጎሪ የሚባለውን ዋና የባሪያ ንግድ ደሴት ተቆጣጠረች። ከዛም በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ቁጥጥሩዋን ወደ መላው ሴኔጋል ማስፋፋት ጀመረች።

በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ.ፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ።

ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ።

ፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች።

አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል።

ምጣኔ ሀብትለማስተካከል

ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣጥጥጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው።

ፖለቲካለማስተካከል

ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል።

ሴኔጋል ከ፹ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ፓርላማዋ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት። አንዱ ፻፳ መቀመጫዎች ያሉት የብሔራዊ ስብሰባ (እንግሊዝኛ፦ National Assembly) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፻ መቀመጫዎች ያሉት ሴኔት ነው። ሴኔጋል ራሱን የቻለ ህግ ተርጓሚ አካል አላት። ዳኛዎቹ የሚሾሙት በፕሬዝዳንቱ ነው።

በአሁኑ ጊዜ ሴኔጋል የዴሞክራሲ ሂደት ስኬታማ ነው ከሚባሉት የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ናት። የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። ማራባውት የሚባሉ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችም በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ ተፅእኖ አላቸው፡

የአመራር ክፍሎችለማስተካከል

ሴኔጋል ወደ 14 ክልሎች ትከፈላለች። የክልሎችና የክልሎች ዋና ከተማዎች ስም ተመሳሳይ ነው።

  • ሉጋ
  • ማታም
  • ሴንት-ሉዊ
  • ሴዲው
  • ቲየስ
  • ታምባካውንዳ
  • ካውላክ
  • ካፍሪን
  • ኬዱጉ
  • ኮልዳ
  • ዚጉዊንቾር
  • ዲዩርቤል
  • ዳካር
  • ፋቲክ





ትላልቅ ከተማዎችለማስተካከል

የሴኔጋል ትላልቅ ከተማዎች

ከ፪ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉበት የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የሀገሩ ትልቁ ከተማ ነው።[1] ሁለተኛው ፭፻ ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ቱባ ከተማ ነው።[1][2]


ከተማየሕዝብ ብዛት (2005 እ.ኤ.አ.)
ዳካር (ዋና ዳካር, ጉዌዲያዋዬ እና ፒኪኔ[2])2,145,193[1]
ቱባ (ቱባ ሞስኪ[2])475,755[1]
ቲዬስ240,152[1]
ካኦላክ181,035[1]
ምቦር170,875[1]
ሴንት ሉዊ165,038[1]
ሩፊስክ154,975[1]
ዚጉዊንቾር153,456[1]

ሕዝብለማስተካከል

ሴኔጋል ከ12.5 ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ አላት። ከዚህ ውስጥም ወደ ፵፪ ከመቶ በገጠር ነው የሚኖረው።

የአሜሪካ የስደተኖች ኮሚቴ ባቀረበው የ2008 እ.ኤ.አ. የዓለም ስደተኞች አጠቃላይ ቅኝት መሠረት ሴኔጋል በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ 23,800 የሚገመቱ ስደተኞች ይኖሩባታል። ከዚህ አብዛኛዎቹ የመጡት ከሞሪታኒያ ነው። ስደተኞቹ በንድዮም፣ ዶዴል እና በሴኔጋል ወንዝ አቅራቢያ በሚገኙ ሠፈሮች ይኖራሉ።[3]

የአገር ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከብዙ ኗሪ ቋንቋዎች 11ዱ በተለይም ዎሎፍኛ አገራዊ ዕውቅና አላቸው። ሌሎቹ ባላንታኛ፣ ማንዲንክኛ፣ ፑላርኛ (ፉላኒኛ)፣ ሰረርኛ፣ ሶኒንክኛ፣ ኖንኛ፣ ማንካኛኛ፣ ማንጃክኛ፣ ጆላኛ እና ሀሣኒያ አረብኛ ናቸው። ፖርቱጊዝኛም በትምህርት ቤት ይማራል፣ የካቦ ቨርዴ እና የጊኔ-ቢሳው ኅብረተሠቦችም ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል ይናገራሉ።

ከሴኔጋል ሕዝብ 94% የእስልምና አማኞች፣ 5% ክርስትና (ባብዛኛው ካቶሊክ)፣ 1% የኗሪ አርመኔነት ተከታዮች ናቸው። የመንግሥት ሃይማኖት የለውም።

በሴኔጋል ልማዳዊ ባሕል ግሪዮት የተባሉ ሽማግሎች ታሪኮቻቸውን በአፍ ቃል ይደግማሉ። ሴኔጋል ለሙዚቃዊ ስልቶቹ ይታወቃል፤ በተለይ የሚወድደው ዘመናዊው ስልት ምባላክስ ተብሏል። በሴኔጋል አበሳሰል በተለይ አሣዶሮበግአተርዕንቁላልበሬ ይጠቀማሉ፤ እስላም አገር እንደ ሆነው መጠን ግን አሳማ አይበላም። ኩስኩስ፣ ሩዝስኳር ድንችምስር፣ ጥቁር-ዐይን አተር ደግሞ በሴኔጋል አበሳሰል በሰፊ ይገኛሉ። በእስፖርት በኩል፣ ከሁሉ የሚወደደው ባህላዊው የሴኔጋል ትግል ግጥሚያ ሲሆን፣ እግር ኳስቅርጫት ኳስ ደግሞ እጅግ ይወደዳሉ።

ማመዛገቢያለማስተካከል

  1. ^ Agence Nationale de la Statistique et de la Démographie (2005 እ.ኤ.አ.). "Situation économique et sociale du Sénégal" (PDF) (በፈረንሳይኛ). Government of Senegal. Archived from the original on 2008-06-25. በ2008-11-18 የተወሰደ.
  2. ^ Forsberg, Jan. "Cities in Senegal" (በእንግሊዝኛ). Archived from the original on 2012-02-27. በ2008-11-18 የተወሰደ.
  3. ^ "World Refugee Survey 2008" (in እንግሊዝኛ). U.S. Committee for Refugees and Immigrants. 2008-06-19. Archived from the original on 2010-05-28. https://web.archive.org/web/20100528032724/http://www.refugees.org/survey/ በ2011-01-23 የተቃኘ. 
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ሴኔጋል የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።


🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchአበበ ቢቂላአንኮር ዋትሥርዓተ ነጥቦችላሊበላየአድዋ ጦርነትየአክሱም ሐውልትዓፄ ቴዎድሮስቅዱስ ያሬድጥላሁን ገሠሠእርዳታ:ይዞታኢትዮጵያቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴየዋና ከተማዎች ዝርዝርModule:Argumentsአፈወርቅ ተክሌአስቴር አወቀአክሱምዳግማዊ ምኒልክኢንዶኔዥያሥነ ምግባርኤችአይቪገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችምሥራቅ አፍሪካአዲስ አበባየጢያ ትክል ድንጋይሙላቱ አስታጥቄጣይቱ ብጡልደራርቱ ቱሉጥሩነሽ ዲባባሐረርገብርኤል (መልዐክ)ጀጎል ግንብአማርኛፋሲል ግቢየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማጥርኝኃይሌ ገብረ ሥላሴቅዱስ ገብርኤልውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌዘጠኙ ቅዱሳንቴሌቪዥንፀደይየኢትዮጵያ ቋንቋዎችመጽሐፍ ቅዱስየጋብቻ ሥነ-ስርዓትማሪቱ ለገሰአክሊሉ ለማ።የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችአሊ ቢራአፈ፡ታሪክትግራይ ክልልዩ ቱብአስናቀች ወርቁዐቢይ አህመድየኢትዮጵያ አየር መንገድየኢትዮጵያ ነገሥታትማርያምልዩ:RecentChangesየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርኬንያየቅርጫት ኳስክረምትፋሲለደስየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግአሸንዳበጋፍቅርሥነ-ፍጥረትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንሀዲያዛጔ ሥርወ-መንግሥትየዮሐንስ ወንጌልዮሐንስ ፬ኛጸጋዬ ገብረ መድህንአማራ (ክልል)ስዕል:Tewodros.Fusela.pdfታሪክመሬትግብረ ስጋ ግንኙነትየኢትዮጵያ ሕገ መንግስትአክሱም መንግሥትየቃል ክፍሎችቅኔንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያእምስብጉንጅጥግእያሱ ፭ኛበላይ ዘለቀባሕልኢየሱስኦሮሞውክፔዲያሀዲስ ዓለማየሁገዳዩ ባልሽ የሞተው ወንድምሽስዕል:Tewodros.Mondon.pdfሚካኤል